ኑ እንሟገት

የቀዳሚ አንባቢ (የዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ) አስተያየት፣
…ወንድማችን የሺሕጥላ ይገዙ የዚህን ስመ ጥር ሊቅ ተወዳጅና ጠቃሚ መጽሐፍ፣ የበኲር ሥራው አድርጎ አቅርቦልናል፡፡
ሙያዊ ቃላት እንደ ልብ በማይገኙበት ሁኔታ ውስጥ ይህን መጽሐፍ በግል ተርጐሞ ለንባብ ማብቃት፣ ለአገሪቱ እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ በረከት ነው፡፡ ሥነ አመክንዮ ለዕቅበተ እምነት፣ ለፍልስፍና፣ ለደርዛዌ ነገረ መለኮት፣ ለሕግ ትምህርት፣ ለፍልስፍናዊ ነገረ መለኮት እጅግ ሲበዛ ወሳኝ የትምህርት ዘርፍ ነው፡፡

ምናልባት ለአንድ ክርስቲያን ከቅዱሳት መጻሕፍት ቀጥሎ እጅግ ጠቃሚ የጥናት ክፍል፣ ሥነ አመክንዮ ነው ቢባል፣ እብለትም ግነትም አይሆንም፡፡ ነገረ መለኮትን የጒዞ መስመሬ አደርጋለሁ፣ በተለይ በዕቅበተ እምነት ጌታን አገለግላለሁ የሚሉ ወገኖች ሁሉ፣ መልሰው መላልሰው ሊያጠኑት የሚገባ መጽሐፍ ነው፡፡
ሥነ አመክንዮ የጠቃሚነቱን ያህል፣ ሲጠና ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ ይህን መጽሐፍ እንደ ልብ ወለድ መጻሕፍት ወይም እንደ ግለ ታሪክ፣ አንድ ጊዜ አንብበን የምንተወው መጽሐፍ
አይደለም፡፡ መርሖው ልባችን እስኪዘልቅ ድረስ፣ ከደም ከሥጋችን ጋር እስኪዋሐድ ድረስ፣ ደግመን ደጋግመን መልሰን መላልሰን ልናነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው፡፡

ከእኛነታችን ጋር ከተዋሐደ በኋላ ግን፣ እንኳን አስተውለነው፣ እንደ ዘበት የሰነዘርነው ዐጸፋ የሐሰትን ግንድ እየከተከተ ሲጥል እናያለን…

$30.08