© Copyright 2020-2024 kulu1.com
ራስ አሉላ አባ ነጋ እና ሰሜን ኢትዮጵያ የታሪክ አሻራቸውና ስብዕናቸው
ለመሆኑ “ፅድቅ እንደ ላሊበላ፣ ፍትሕ እንደ አሉላ” እየተባለ ይነገርላቸው ስለነበሩት ራስ አሉላ አባ ነጋ (ወዲ ቑቢ) ትውልድ፣ ዕድገት፣ አነጣጥሮና አልሞ ተኳሽነት፣ ወታደርነት፣ አገራዊነት፣ ለጠላት አይበገሬነት፣ ጀግንነት፣ የጦር ሜዳ ውሎ፣ የጦርነት ጥበብ፣ ዲፕሎማሲያዊ ብልህነት፣ ትኩርነትና ስብዕናቸው በተመለከተ ምን ያውቃሉ?
‘ራስ አሉላ አባ ነጋ (ወዲ ቑቢ) እና ሰሜን ኢትዮጵያ’ የተሰኘ መጽሐፍ በሁለት ቅጽ ተዘጋጅቶ ሁለት ትላልቅ መጻሕፍት እንደ አንድ ሆነው የታተሙ ሲሆን እነዚህ ሁለት ቅጾች የራስ አሉላ አባ ነጋ ጀግንነቶችንና የጦር ሜዳ ውሎዎችን ብቻ የሚዳስሱ ሳይሆኑ የታሪክ አሻራቸውና ስብዕናቸውን ጭምር በጥልቀት የሚዳስሱና የሚተነትኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጻፉ ጥልቅ የታሪክ ድርሳናት ናቸው። እነዚህ በሁለት ቅጾች ተዘጋችተው የታተሙ መጻሕፍት ራስ አሉላ አባ ነጋ (ወዲ ቑቢ) ከተወለዱበት ከ1819 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ከዚህ ዓለም ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ 1889 ዓ.ም ድረስ ከዕድገታቸው እስከ ህልፈታቸው የነበራቸውን ታሪክ፣ ጀግንነት፣ ወታደራዊ ብቃታቸውና ጥበባቸው፣ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶቻቸውና በአጠቃላይ ስብዕናቸውን የሚዳስሱ በመሆናቸው ከአፄ ዮሐንስ ፬ኛ ጋር በነበራቸው ቅርበትና የመረብ ምላሽ ምድረ ሐማሴን ባህረ ነጋሽ ጠቅላይ ገዥነታቸው ምክንያት በተገቢው መንገድ ተዳስሰዋል። የአፄ ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ የነበራቸው ስብዕናም በነዚሁ ሁለት መፃሕፍት በሚገባ ተፈትሸዋል። ራስ አሉላም ሆኑ አጼ ዮሐንስ ፬ኛ በዘመነ መሣፍንት የመጨረኛ ሁለትና ሦስት ዓሰርት ዓመታት አካባቢ የተወለዱ በመሆናቸውና ከዕድገቶቻቸው ጋር የተገናዘበ ስነ ልቦናዊ ስብእናዎቻቸውን ለመረዳትና በትግራይ ትግርኚ የነበረውን ታሪካዊና ማሕበረሰባዊ ክስተቶችን ለመገንዘብ እንዲረዳ ሲባል የእነዚህ መጻሕፍት የትኩረት ጅማሬ ከዘመነ መሣፍንት እንዲሆን በመደረጉ የትግራይ ትግርኚ መሣፍንትና መኳንንት ከጎንደር ነገሥታት ጋር የነበራቸውን ቁርኝትና ትስስርን በሚያሳይ መልኩ ታሪካዊ ዳራን ለማሳየት በጥንቃቄ ትኩረት ተደርጓል።
የዘመነ መሣፍንት ባላባታዊ ሥርዓት ከትግራይ ትግርኚ ታሪካዊና ማኅበረሰባዊ ትስስሮች ጋር ተገናዝቦ እንዲታይ በመደረጉ በተለይም በትግራይ ትግርኚ ግዛት ውስጥ ስለነበረው የደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ገብሬ ዘመነ አገዛዝና የተካሄዱ ጦርነቶች በመፈተሻቸው በዚሁ ጊዜ ስለነበረው ስነልቦና በበቂ መልኩ ታሪካዊ ዳሰሳ ተደርጓል። የራስ አሉላ አባ ነጋ ጀግንነትና ስብዕና መነሻው ከተወለዱበት የትግራይ አካባቢ ሲሆን ከውጭ ጠላቶች ጋር ያካሄዷቸው 12 ጦርነቶች የመሩበትና ለድል የበቁባቸው የጀግንነት ጥበቦች ተተርከዋል። የኢጣሊያ ጦር ወደ ምፅዋዕ መምጣትና ከመረብ ምላሽ ግዛት በወረራ መያዝ ጋር ተያይዞ በተለይም የውጫሌ ውል መፈረምና የመተማ ጦርነትን ተከትሎ በተፈጠሩት የታሪክ አጋጣሚዎች የአሁኒቷ ኤርትራ እንዴት እንደተፈጠረች በነዚህ መጻሕፍት ይነበባሉ። የራስ አሉላ አባ ነጋ የሀገር ፍቅር ስሜትና ለማንም የውጭ ጠላት ሆነ ለአገር ውስጥ ጠብአጫሪዎች የማይበገሩ ስለመሆናቸው ሲታይ እስከ ዛሬ ድረስ መተኪያም ተተኪም የሌላቸው ለአሁኑ ወጣት ትውልድ አርአያ ስለመሆናቸው ሁሉም ይመሰክርላቸዋል። አፍሪካዊው የጦር ጀነራል ስለተባሉት ትግራዋይ ኢትዮጵያዊ ራስ አሉላ አባ ነጋ ታሪክ፣ ጀግንነትና ስብዕናቸውን ለማወቅም ለመረዳት እነዚህም ሁለት ቅጽ መጻሕፍት በጥልቀት ያንብቡ። መልካም ንባብ ይሁንልዎ!!!
$35.93

Description

Reviews (0)
Only logged in customers who have purchased this product may leave a review.
More Offers
No more offers for this product!
Reviews
There are no reviews yet.