ኑ! እናስብ
…ሰዎች ለምን በውሳኔዎቻቸው ይሳሳታሉ? ለምን ይሆን በአስተሳሰባቸው የማያስፈልግ ነገር የሚታየው? ለምንስ ነው
ተፋልሶ የሚፈጽሙት? እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እንድንጠይቅ የሚያደርገን የሰዎች አስተሳሰብ መጥራት በሚገባው ልክ አለመጥራቱ ነው።
ስለ ተፋልሶና በአጠቃላይ ስለ አመክንዮ (ምክንያታዊነት)
በማንበብና ጽሑፍ በማዘጋጀት ላይ እያለሁ በአንዳንድ ጽሑፎች
የተፋልሶ ወይም በዐረፍተ ነገራዊ ብይን የሚታየው ስሕተት ምንጩ
ያልጠራ የሰዎች አመለካከት እንደሆነ ማየቴ ይህንና ከዚህ በኋላ
ተከታትለው የሚወጡትን መጻሕፍት እንድጽፍ አነሳስቶኛል።
$22.12
